ራስዎንና ሌላውን በሽታ ከማስተላለፍ ይከላከሉ

ርቀት ይጠብቁ

በቤት ውስጥ ሆነ ከቤት ውጭ ከሌላ ስው ጋር የሚኖርዎትን ርቀት ይጠብቁ፥ በተጨናነቀ አካባቢ ውስጥ ከመገኘት ይቆጠቡ።

ይህ ማሳሰቢያ በማንኛውም ወቅት የሚፀና ነው፥ ይህም ማለት አንዳንድ ነገሮች ለመሸመት ወደ ገበያ ቦታ ሲሄዱ ብቻዎን መሆን፣ በቅርብዎ ካሉ ሰዎች ጋር በቀር ማህበራዊ ስብሰባ ከማድረግ መቆጠብ፥ ሥራዎን እቤት ውስጥ ሆነው መስራትና መጓዝ ካለብዎት ደግሞ በተቻለ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከመጠቀም መቆጠብ ማለት ነው።

ህመምዎ አነስተኛ ቢሆንም፥ የህመም ምልክት ከተሰማዎት ከቤት አይውጡ፥ ምርመራም ያድርጉ።

ልጆችም ሆኑ አዋቂዎች ሲታመሙ ከቤት መውጣት የለባቸውም፥ ከሥራ፥ ከትምህርት ቤት፥ ከመውዓለ ሕፃናትና ከሌሎችም የእንቅስቃሴ ቦታዎች መቅረት ይኖርባቸዋል። የህመሙ ምልክቶች አነስኛ ሆነው ቢታዩም ይህ መተግበር አለበት። ህመም ሲሰማውት ምርመራ ማድረግና ከሌሎች ጋር ከመገኛኘት መቆጠብ አለብዎት።

ሥራዎን እቤትዎ ውስጥ ሆነው ያከናውኑ

የሕዝብ ጤና ጠበቃ ባለሥልጣን (Folkhälsomyndigheten) ከቤታቸው ሆነው ሥራ መስራት የሚችሉትን ሁሉ፥ ሥራቸውን እቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ ያሳስባል። ሥራዎን እቤትዎ ውስጥ ሆነው ማከናወን ይችሉ እንደሆን አሰሪዎን ይጥይቁ። እቤት ውስጥም ቢሆን አሰሪዎ የሥራ ቦታው አመቺ እንዲሆን የበኩሉን ሃላፊነት መወጣት ይጠበቅበታል።

ከጥቂት ሰዎች ጋር ብቻ ይዋሉ፥ አካላዊመቀራረብ ከማድረግ ይቆጠቡ

የኮቪድ-19 ስርጭት ጠንቅ፥ ብዙ ሰዎች እየተገናኙ በሄዱ ቁጥር እየጨመረ እንደሚሄድ የተረጋገጠ ነው። ግንኙነትዎን በቅርብዎ ካሉት ቤቴሰቦችዎ ወይም ከጥቂት ወዳጅዎችዎ ወይም ከቤት ውጭ ደግሞ ግንኙነትዎን ከጥቂት የቅርብ ሰዎችዎ ጋር ብቻ በማድረግ የሚገናኟቸውን ሰዎች ቁጥር ገደብ ሊያደርጉበት ይችላሉ።

ከቻሉ ከቤት ውጭ ሰዎችን መገናኘት ምንም አይደለም፥ ቢሆንም ግን ወዲያውኑ በመሃላችሁ ትልቅ ርቀትእንዲኖር ያድርጉ።

እድሉን ካገኙ ክትባት ይውሰዱ

ክትባት መውሰድ በኮቪድ-19 በፅኑ ከመታመም እንዲሁም በበሽታው ታምመው የመሞት መዘዝን ይቀንሳል። ከ18 ዓመት እድሜ በላይ ያለ ሁሉ የመከተብ እድል ይሰጣቸዋል። በሕዝብ ጤና ጥበቃ ባለሥልጣን (Folkhälsomyndighetens) ድረገጽ ላይ ስለ ክትባቱ አሰጣጥ መረጃ ያገኛሉ። ክትባቱንየመውሰድ ወይም አለመውሰድ ውሳኔ የግልዎ ፈቃደኝነት የሚመለከት ጉዳይ ነው፥ የሕዝብ ጤና ጥበቃ ባለሥልጣን ክትባት መውሰድ የሚችሉ ሁሉ የክትባት ግብዣውን በአዎንታ እንዲቀበሉ ይመክራል። በሚኖሩበት አካባቢ የክትባት አስጣጡ ሂደት እንዴት እንደተዘጋጀ ለማውቅ በ
1177.seድረገጽላይ ማንበብ ይችላሉ።

እጆችዎን አዘውትረው ይታጠቡ

የበሽታው ህዋሳት እጅ ላይ በቀላሉ ልክክ የማለት ባህሪ አላቸው። ይህም ማለት ለምሳሌ፥ እጅዎ በበሽታው ህዋሳት የተበከለ ከሆነና በዚህ እጅዎ ሌላ ሰው ቢነኩ ህዋሳቱ ወደ ሌላው ይተላለፋል። ስለዚህ እጆችዎን በሙቅ ውሃና በሳሙና ቢያንስ ለ20 ደቂቃ በደንብ ይታጠቡ።
እጆችዎን ሁሌ መታጠብ ያለብዎት ግዜ፣

  • እቤትዎ ሲገቡ ወይም የስራ ቦታዎ ውስጥ ሲገቡ
  • ደጅ ቆይተው ከሆነ
  • ለመመገብ ወደ ማእድ ሲቀርቡ
  • ምግብ ሲያዘጋጁ
  • ከመፀዳጃ ቤት ሲወጡ

እጆችዎን የመታጠብ እድል በማይኖርበት ወቅት የእጅ አልኮል (ወይም ተማሳሳይ ህዋሳት ማምከኛ ፈሳሽ) እንደ አንድ አማራጭ መጠቀም ይቻላል።

በተጨማሪም የበሽታው ህዋስ ወደ ውስጥ አካላት እንዳይገባ በእጅዎ ዓይኖችዎን፥ አፍንጫዎንና አፍዎን አይንኩ። እንዲሁም በሚያነጥሱበት ወይም በሚስሉበት ግዜ የክንድዎ መታጠፊያ ላይ ወይም የወረቀት መሃረብ እንዲከናወን ያድርጉ���

እንቅስቃሴዎ በሽታውን ከማስተላለፍ የፀዳ ይሁን

ራስዎንና ሌላውን ከኮቪድ-19 ለመከላከል፥የተቻልዎትን ሁሉ በማድረግ ስርጭቱን የመግታት ግዴታ አለብዎት። ራስዎን ከቫይረሱ መከላከል፥ ርቀትዎን መጠበቅ፥ ወረርሽኙ ወደ ሌላ ሰው እንዳይተላለፍ ማሰብ ያለብዎት እርሶ ራስዎ ነዎት። ለሌላው ሰው ደህንነት ማሰብ ይኖርብዎታል። ይህ ነጥብ በተለይ በወረርሽኙ ክፉኛ ሊጠቁ የሚችሉ ሰዎች ላይ በእጅጉ ሊታሰብበት ይገባል።